ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ በእስር ላይ የሚገኙ አባሎቹ እንዲፈቱ ጠየቀ
HR REPORTS
በቅርቡ የተመሠረተው የጎጎት ፓርቲ አመራሮች፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በፓርቲው የምሥረታ ጉባኤ ማግሥት፣ ምክትል ሊቀ መንበሩን ጨምሮ በዐዲስ አበባ ከተማ በጸጥታ ኀይሎች የተያዙ 12 አባሎቹ በደቡብ ክልል ታስረው እንደሚገኙ ገልጸው፣ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
የጎጎት ፓርቲ በዛሬ መግለጫው ያሰማውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ከደቡብ ክልል ፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡
በተጨማሪም፣ ጋዜጠኞችን ጨምሮ የጉራጌን የክልልነት ጥያቄ ያነሡ በርካታ ግለሰቦች እንደታሰሩ መኾናቸውን የጎጎት አመራሮች ገልጸዋል፡፡
የተጀመረው የክልልነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ፣ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ፓርቲው አስታውቋል