የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለውጥ እንደማይመጣ ገለጹ

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለውጥ እንደማይመጣ ገለጹ

የዜና ትንታኔ

8/23/2023

ዐሥራ አንድ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙበት የመካሮች ስብስብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ብቻ ሊፈታ እንደማይችል በመጥቀስ፣ በዐማራ ክልል በትግበራ ላይ ያለውን ዐዋጅ ተቃወመ።

የመካሮቹ ስብስብ(Caucus) አባል የኾኑና የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ መፍትሔ ያመጣበት የታሪክ አጋጣሚ እንዳልነበረ አውስተዋል፡፡ ይልቁንም፣ በዘፈቀደ የኀይል ርምጃ ችግሮችን እንደሚያባብስ አሳስበዋል፡፡

ዘርፈ ብዙ እና እጅግ አሳሳቢ ሲሉ ለገለጹት የኢትዮጵያ ችግር፣ በፖለቲካዊ ውይይት መፍትሔ ሊገኝ እንደሚችል ያመለከቱት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በአንጻሩ መንግሥት፣ ለሐቀኛ ፖለቲካዊ ውይይት ዳተኛ እንደኾነ ተችተዋል፡፡

በአንጻሩ መንግሥት፣ የተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎቹን ትችቶች፣ በተደጋጋሚ ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡